የልቤ ፡ አምላክ (Yelebie Amlak)

አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)

እንደ ፡ ጥል ፡ ሆንክልኝ ፡ እንደ ፡ አበባ ፡ አበብኩኝ
እንደ ፡ ሊባኖስ ፡ ፍሬ ፡ በቤትህ ፡ ሥር ፡ ሰደድኩኝ
እንደ ፡ ወይራ ፡ በበግ/ሸታ ፡ እንደ ፡ መዓዛዉ
በእኔ ፡ ያስቀመጥከው ፡ ዓለምን ፡ ሞላዉ (፪x)

አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)

እንደ ፡ ዘንባባ ፡ ዛፍ ፡ እያሳደገኝ
ፍሬን ፡ አበዛው ፡ አለመለመኝ
እንደ ፡ ረካች ፡ ገነት ፡ አምላኬ ፡ አደረገኝ
በብዛት ፡ በብዛት ፡ በብዛት ፡ ባርኮኝ

አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)

እንደ ፡ ጠዋት ፡ ፀሐይ ፡ እንደሚያበራዉ
የጻድቃንም ፡ መንገድ ፡ እንደዚሁ ፡ ነዉ
ሙሉ ፡ ቀን ፡ እስኪሆን ፡ ገና ፡ ይጨምራል
የእኔም ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ እነሆ ፡ እንዲህ ፡ ሆኗል

አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x)

በውኑ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ
የሥጋ ፡ ለባሽ ፡ አምላክ ፡ የሚያቅተው ፡ አለ ፡ ወይ (፪x)

ልቤ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጸና (፬x)
እርሱን ፡ ተማመነ ፡ ሆሆ ፡ እርሱን ፡ ተማመነ (፪x)

በውሃው ፡ ላይ ፡ እየተረማመደ ፡ እየተረማመደ
ለሚፈሩ ፡ እምነትን ፡ አስለመደ (፪x)

ማዕበሉም ፡ ወጀቡም ፡ የሚታዘዝለት
ይሄ ፡ ማነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue