Fitih Enkerbalen Yihew Zare (ፊትህ ፡ እንቀርባለን ፡ ይኸው ፡ ዛሬ)

አዝ፦ በረሃ ፡ ነው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ
ውስጡ ፡ ግን ፡ አበበ ፡ ጽጌሬዳ
በደስታ ፡ በሃሴት ፡ በዝማሬ
ፊትህ ፡ እንቀርባለን ፡ ይኸው ፡ ዛሬ (፪x)

ማን ፡ ተስፋ ፡ ያደርጋል ፡ ጽጌሬዳ
ጨው ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ
እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ሲያስተካክለው
አይቻለሁ ፡ አኔ ፡ ለበጐ ፡ ነው (፭x)

አዝ፦ በረሃ ፡ ነው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ
ውስጡ ፡ ግን ፡ አበበ ፡ ጽጌሬዳ
በደስታ ፡ በሃሴት ፡ በዝማሬ
ፊትህ ፡ እንቀርባለን ፡ ይኸው ፡ ዛሬ (፪x)

አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ተሟጠጠ
ቢመስለኝ ፡ ያለቀ ፡ የተቆረጠ
በጊዜው ፡ መጥቶ ፡ ውብ ፡ አድርጐታል
ለእግዚአብሔር ፡ ምንድን ፡ ይሳነዋል (፭x)

አዝ፦ በረሃ ፡ ነው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ
ውስጡ ፡ ግን ፡ አበበ ፡ ጽጌሬዳ
በደስታ ፡ በሃሴት ፡ በዝማሬ
ፊትህ ፡ እንቀርባለን ፡ ይኸው ፡ ዛሬ (፪x)

ምንተስኖህ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ያቅትሃል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ይቻልሃል
ታላቁን ፡ ተራራ ፡ ስትንደው
የተመለከተ ፡ ምስክር ፡ ነው (፭x)

አዝ፦ በረሃ ፡ ነው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ
ውስጡ ፡ ግን ፡ አበበ ፡ ጽጌሬዳ
በደስታ ፡ በሃሴት ፡ በዝማሬ
ፊትህ ፡ እንቀርባለን ፡ ይኸው ፡ ዛሬ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue