Ye Hayalan Hayal Yegna Geta (የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ)

አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ
በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የሆነ/የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም
ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)

ብዙ ፡ ሃያላኖች ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ነበሩ
እንድ ፡ ዘመን ፡ ታይተው ፡ ጠፍተው ፡ በዚያው ፡ ቀሩ
የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሎ
ከበረ ፡ በሰማይ ፡ አሜን ፡ በሞት ፡ ላይ ፡ አይሎ

አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ
በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም
ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም

የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
ማነው ፡ የሚመስለው ፡ የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስ
ማህተቡን ፡ ሊፈታ ፡ የቻለው ፡ እርሱ ፡ ነው
ይክበር ፡ ዛሬም ፡ አሜን ፡ አዎ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ
በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን/የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም
ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)

ማንም ፡ ያልቻለውን ፡ መጋረጃ ፡ ቀዶ
ወንጌልን ፡ ሰበከ ፡ ወደ ፡ ሲኦል ፡ ወርዶ
ለታሰሩት ፡ ሰላም ፡ መፈታት ፡ አወጀ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ በደሙ ፡ እኛን ፡ ዋጀ

አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ
በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም
ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም

የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ
በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ ኃያል ፡ ንጉሥ
እንደ ፡ አንተ ፡ የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም
ክበር ፡ ንገሥ ፡ ለዘላለም

አጋንንት ፡ በሥሙ ፡ ይታዘዙለታል
ሰማይ ፡ ምድር ፡ ሁሉ ፡ ለክብሩ ፡ ዝቅ ፡ ይላል
ማዕበል ፡ ወጀቡን ፡ ባሕሩን ፡ ይከፍላል
ጌት ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ አዎ ፡ ዘለዓለም ፡ ይገዛል

አዝ፦ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ
በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም
ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)

እንደ ፡ እርሱ ፡ የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም
ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም
እንደ ፡ አንተ ፡ የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም
ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue