Meserete Kirstos Choir--Endet Dink Amlak New--BeMezmur Wodase (በመዝሙር ፡ ውዳሴ)

ቀናትም ፡ ያልፉና ፡ ዘመን ፡ ተፈፅሞ
የክርስቲያን ፡ ፈተና ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አብቦ
በጥፋት ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ መኖር ፡ ያበቃና
የዓይናችንን ፡ እንባ ፡ ጌታም ፡ ይጠርግና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አዛር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ ዕልልታ
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይክብርና ፡ ምሥጋና

መች ፡ ይላል ፡ ተመሥገን ፡ ጊዜው ፡ ይደርስና
ከልቡ ፡ አልቅሶ ፡ ለጌታው ፡ ይነግርና
ምኞቱም ፡ ጥረቱም ፡ መቼ ፡ ይሳካና
ጌታን ፡ ሲል ፡ ይሰማል ፡ በድሆች ፡ ተፅናና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አዛር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ ዕልልታ
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይክብርና ፡ ምሥጋና

አእላፋት ፡ ፃድቃን ፡ ከምድር ፡ እንሄድና
ነጭ ፡ ልብሳችን ፡ ለብሰን ፡ ዙፋን ፡ እንከብና
ኪሩቤል ፡ ላይ ፡ ላለው ፡ ለበጉ ፡ እንሰግድና
መች ፡ እንዘምር ፡ ይሆን ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አዛር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ ዕልልታ
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይክብርና ፡ ምሥጋና

የምድር ፡ መፃተኛ ፡ ልብህ ፡ የተሰቀለ
ጥማትን ፡ ለማየት ፡ ተስፋ ፡ ያልጐደለህ
መቼ ፡ ቀን ፡ ሞልቶልን ፡ ፅዮን ፡ ትደርስና
ጌታን ፡ በዓይንህ ፡ አይተህ ፡ ልብህ ፡ ይረካና

አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአሥራ ፡ ሁለት ፡ አዛር ፡ በታላቅ ፡ በገና ፡ ምሥጋና ፡ ዕልልታ
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያው ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይክብርና ፡ ምሥጋና

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue