Na Getta (ና ፡ ጌታ)

ሕዝብህ ፡ ይጠብቅሃል ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
መገለጥህ ፡ ናፍቆታል ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
እባክህ ፡ ናልኝ ፡ ሳትቆይ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ ? ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!

አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ?

ስምህን ፡ ስለወደደች ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
ነፍሴ ፡ ስድብን ፡ ጠገበች፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታዬ ፡ ሆይ!
ባርኮቷን ፡ እያሰበች፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
ዛሬም ፡ በአንተ ፡ ታምናለች፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!

አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ?

ድካሙ ፡ ሳይበረታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
አርበኛው ፡ ሳይረታ፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
የተጋዳይ ፡ አለኝታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
በጠላትህ ፡ ላይ ፡ በርታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!

አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ?

ጣኦቱ ፡ ተሰባብሮ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
ልመልከት ፡ ስምህ ፡ ከብሮ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
ከጥንት ፡ እንደታወቅህ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!
ምድር ፡ አንተን ፡ ትወቅ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ!

አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ?

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue