Bemejemeria (በመጀመሪያ)

በመጀመሪያ ፡ በመጀመሪያ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፪x)

ሳይወድ ፡ በግዱ ፡ ይመጣል
የልቤ ፡ መሻት ፡ ይሆናል
እንደተጻፈው ፡ አደርጋለሁ
በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

ሰው ፡ ባለው ፡ በሃብቱ ፡ ምን ፡ ቢኮራ
ቢማር ፡ ሊቅ ፡ ቢሆን ፡ ታሪክ ፡ ቢሰራ
ጌታ ፡ ከሌለው ፡ ግን ፡ ባዶ ፡ ነው
በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፪x)

ዳዊትም ፡ ኖረ ፡ እድሜ ፡ ዘመኑን
መጀመሪያ ፡ አርጐ ፡ እግዚአብሔርን
የሚቋቋመው ፡ አልነበረም
መንግስቱ ፡ ጸና ፡ ለመለመ

የእግዚአብሔር ፡ ልቡ ፡ እንዳረፈበት
እንደልቤ ፡ እንዳለው ፡ እንደኮራበት
እንደእምነት ፡ አባቴ ፡ እንደዳዊት
አስደስታለሁ ፡ የጌታን ፡ ልብ

አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፬x)

Baru-baru ini Didengarkan oleh

0 komentar
    Tidak ada komentar yang ditemukan

:: / ::
::
/ ::

Antre