Bante New Menorie (በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ)

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፪x)

ለምን ፡ እፈራለሁ ፡ እንዴትስ ፡ እሰጋለሁ (፪x)
የዘለዓለም ፡ ኪዳን ፡ ከአንተ ፡ ተቀብያለሁ (፪x)
ዘመናቴን ፡ ቆጥረህ ፡ አውቀሃል ፡ እርምጃዬን (፪x)
ትላንትም ፡ አይቆጨኝ ፡ ነገም ፡ አያስፈራኝ (፬x)

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፪x)

በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ በነፍሴ ፡ የተጻፈው (፪x)
በዓመታቶቼ ፡ ላይ ፡ ክብርህ ፡ የተገለጠው (፪x)
ድንቅ ፡ ተዓምራትህ ፡ ቃላትም ፡ የማይገልጸው (፪x)
መኖሬ ፡ እራሱ ፡ ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፪x)

ምህረት ፡ ቸርነትህ ፡ እየተከታተሉኝ (፪x)
የሥምህ ፡ ጉልበቱ ፡ ከሞት ፡ ስላስጣለኝ (፪x)
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥምህን ፡ እጠራለሁ (፪x)
በሕያዋን ፡ አገር ፡ በፊትህ ፡ እኖራለሁ (፪x)
ቤትህ ፡ እኖራለሁ (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፫x)
ቢረዳልኝ ፡ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ፡ ልቤ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue