Temsgen (ተመስገን )

አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x)

እንደ ፡ እናት ፡ በጀርባ ፡ አዝለህ ፡ አሳደግከኝ
ክፉም ፡ እንዳይነካኝ ፡ በእጅግ ፡ ሰወርከኝ
ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ ፡ ሞገሴ ፡ ሆንክልኝ
እኔም ፡ ዝም ፡ አልልም ፡ ለአንተ ፡ አዜማለሁኝ

አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x)

ሁልጊዜ ፡ ሳስበው ፡ ለኔ ፡ ያደረከውን
ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ አንተን ፡ ለማመስገን
በብዙ ፡ ሃጥያቴ ፡ ዘወትር ፡ ሳስቸግርህ
በፊትህ ፡ አልጣልከኝም ፡ አምላኬ ፡ አቆመኝ ፡ ምህረትህ

አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x)

ብዙ ፡ ማይታለፍ ፡ ተራራ ፡ ሸለቆ
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ያሳለፍከኝ ፡ እኮ
እኔስ ፡ የአንተ ፡ ውለታ ፡ ከልቤ ፡ አይጠፋም
ሁሌ ፡ አዜመዋለሁ ፡ ላፍታ ፡ ዝም ፡ አልልም

አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፬x)

ለዓለም ፡ ለሚመጣው ፡ ትውልድ ፡ አወራለሁ
ያደረክልኝን ፡ እመሰክራለሁ
ብዙ ፡ ዘመናትን ፡ ወራት ፡ ዓመታትን
በእራሴ ፡ አይደለም ፡ ያለፍኩት ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ተመስገን

አዝ፦ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ ተመስገን (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue