Endetekebelkut Mihret (እንደተቀበልኩት ፡ ምህረት)

አዝ፦ እንደ ፡ ተቀብልኩት ፡ ምህረት
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዛት
እንዳገለግልህ ፡ እርዳኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስጠኝ ፡ የመንፈስህን ፡ እሳት

እስራቴን ፡ ቆርጠህ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰብረሃል
ነፍሴ ፡ እንድታከብርህ ፡ ነጻ ፡ አውጥተኸኛል
ባርነት ፡ አበቃ ፡ ልጅ፡ ነህ ፡ ብለኸኛል
በደምህ ፡ ቃልኪዳን ፡ የአንተ ፡ አድርገኸኛል

አዝ፦ እንደ ፡ ተቀበልኩት ፡ ምህረት
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዛት
እንዳገለግልህ ፡ እርዳኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስጠኝ ፡ የመንፈስህን ፡ እሳት

የተፍገመገመ ፡ ከውድቀት ፡ እንዲተርፍ
የደከመን ፡ ሁሉ ፡ በቃልህ ፡ እንድደግፍ
አንቃኝ ፡ በማለዳ ፡ ቀስቅሰኝ ፡ ከእንቅልፍ
ታማኝ ፡ ሎሌ ፡ አድርገኝ ፡ ልብን ፡ የሚያሳርፍ

አዝ፦ እንደ ፡ ተቀበልኩት ፡ ምህረት
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዛት
እንዳገለግልህ ፡ እርዳኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስጠኝ ፡ የመንፈስህን ፡ እሳት

ስንፍናዬን ፡ አርቅ ፡ በተግሳፅህ ፡ በትር
እንድተጋ ፡ እርዳኝ ፡ ከፀጋህ ፡ ዙፋን ፡ ሥር
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ብዬ ፡ እንድመሰክር
ሕይወቴን ፡ ሙላልኝ ፡ በመስቀልህ ፡ ፍቅር

አዝ፦ እንደ ፡ ተቀበልኩት ፡ ምህረት
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዛት
እንዳገለግልህ ፡ እርዳኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስጠኝ ፡ የመንፈስህን ፡ እሳት

ጥበብ ፡ ለሌላቸው ፡ ለማያስተውሉ
ለተማሩም ፡ ሰዎች ፡ አውቀናል ፡ ለሚሉ
ወንጌሉን ፡ ልናገር ፡ እንዲድኑ ፡ አምነው
ለእነዚህ ፡ ሁሉ ፡ ዕዳዬ ፡ ትልቅ ፡ ነው

አዝ፦ እንደ ፡ ተቀበልኩት ፡ ምህረት
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዛት
እንዳገለግልህ ፡ እርዳኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስጠኝ ፡ የመንፈስህን ፡ እሳት

ወንጌል ፡ አይቆጠብ ፡ አይወሰን ፡ በክልል
እስከ ፡ ምድር ፡ ዳር ፡ ይሂድ ፡ ቃልህ ፡ ሳይከለከል
ለቅርቡ ፡ ለሩቁ ፡ ጽድቅህም ፡ ይታደል
ኢየሱስን ፡ አግኝቶ ፡ ፍጥረት ፡ እሰይ ፡ ይበል

አዝ፦ እንደ ፡ ተቀበልኩት ፡ ምህረት
እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ ብዛት
እንዳገለግልህ ፡ እርዳኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስጠኝ ፡ የመንፈስህን ፡ እሳት

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue