ጌታ ፡ ሲናገር (Gieta Sinager) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

የደረቁ ፡ አጥንት ፡ ተስፋ ፡ የሌላቸው
ለክብር ፡ ሆኑ ፡ ዛሬ ፡ ለምልመው
ያለቀ ፡ ጉዳይ ፡ የሞተ ፡ ነገር
ሕይወት ፡ ያገኛል ፡ ጌታ ፡ ሲናገር

ጌታ ፡ ጌታ ፡ ሲናገር (፬x)

እጄን ፡ ባፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል
ጌታ ፡ ለኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል
ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ
ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ (፪x)

ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልርሳ
ለእኔ ፡ የሆነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ምነው ፡ ዘወትር ፡ ቃሎቼ ፡ በዝተው
ጌታን ፡ ባመልከው

ጌታን ፡ ባመልከው (፬x)

ከፊቴ ፡ ይሰበር ፡ የብረት ፡ መዝጊያ
ጠንካራ ፡ አላውቅም ፡ ከኢየሱስ ፡ ወዲያ
አውቆ ፡ ይከፈታል ፡ ኃይልም ፡ አልጨርስ
ሥሙ ፡ ሲጠራ ፡ የአዳኜ ፡ ኢየሱስ

ኢየሱስ ፡ አዳኜ ፡ ኢየሱስ (፬x)

እጄን ፡ ባፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል
ጌታ ፡ ለኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል
ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ
ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለኔ ፡ ሞቶ (፪x)

ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልርሳ
ለእኔ ፡ የሆነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ምነው ፡ ዘወትር ፡ ቃሎቼ ፡ በዝተው
ጌታን ፡ ባመልከው

ጌታን ፡ ባመልከው (፬x)

እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥ ፡ በሬን ፡ ዘግቼ
እንባም ፡ አይወጣኝ ፡ ሞቱን ፡ ሰምቼ
መቃብር ፡ ከፍቶ ፡ ድንጋይ ፡ ፈንቅሎ
ተነሳ ፡ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ተብሎ

ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ተብሎ (፬x)

እጄን ፡ ባፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል
ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ
ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ (፪x)

ዝናህን ፡ ከሩቅ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ሥራ
ሁሉም ፡ ሲያወራ
ሰምቼ ፡ አልቀረሁ ፡ እንዲያው ፡ በወሬ
አየሁህ ፡ ዛሬ

አየሁህ ፡ ዛሬ (፬x)

እጄን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል
ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ
ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue