Ewedihalehu Geta eyesus (እወድሃለሁ ፡ ጌታ)

(እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ) (፪x)

በኃጢአቴ ፡ ሙታን ፡ በነበርኩ ፡ ጊዜ ፡ ሳላይህ ፡ ያየኸኝ
ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ሀይወትን ፡ ፡ ሰጠኸኝ
እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ልዘርጋ ፡ እንጂ
አንተ ፡ የፍቅር ፡ ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ የማያልቅ ፡ ፍቅርህ ፡ አያረጂ

ከአስፈሪው ፡ ነበልባል ፡ እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ከገሃነም ፡ ዳንኩኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ
እኔም ፡ እንደ ፡ ጻድቃን ፡ እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ጸድቀሃል ፡ ተባልኩኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ ጌታ

በኃጢያቴ ፡ ምክንያት ፡ የሞትኩኝ ፡ ነበርኩኝ
እኔም ፡ በእግዚአብሔር ፡ በአምላኬ ፡ ታሰብኩኝ
የመርገም ፡ ጨርቄን ፡ ከላዬ ፡ ገፈፈው
ጽድቅን ፡ አለበሰኝ ፡ (የሚከሰኝ ፡ ማን ፡ ነው) (፪x)

አዝ
እወድሃለሁ ፡ ጌታ

እግዚአብሔርም ፡ ከወደደን ፡ ከትልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ ፡ በኃጢአታችንና ፡ በበደላችን ፡ ሙታን ፡ በነበርን ፡ ጊዜ
ከክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ሰጠን ፡

ሰው ፡ ዞር ፡ ብሎ ፡ አያየኝ ፡ ቢሆንማ ፡ ኑሮ ፡ ምህረት ፡ በሰው ፡ እጅ
እንኳን ፡ ለጽድቅ ፡ ልሆን ፡ እንኳን ፡ ለሌላው ፡ ሰው ፡ ለራሴም ፡ አልበጅ
ዓይኑ ፡ እንዳየች ፡ ሳይሆን ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማች ፡ ሳይፈርድ ፡ አጸደቀኝ
ኧረ ፡ ይገርማል ፡ ኧረ ፡ ይገርማል ፡ ሰዎች ፡ እኔንም ፡ አዳነኝ
የማይገባኝን ፡ እወድሃለሁ ፡ጌታ ፡ የሕይወትን ፡ አክሊል ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ
በነጻ ፡ ሰጠኸኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ስምህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ እውድሃለሁ ፡ የሱስ

አዝ



(እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ ፡ የሱስ) (፪x)

최근에 들은 사람

0 코멘트
    댓글이 없습니다

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

대기줄