ክብርህን ፡ አይ ፡ ዘንድ ፡ እሻለሁ
ረሃቤ ፡ ጥማቴ ፡ ይኸው ፡ ነው
ሞገስ ፡ ካገኘሁኝ ፡ በፊትህ
ለምኜ ፡ እንድቀበል ፡ ከፈቀድህ
እንድ ፡ ጥያቄ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ ያለኝ
ጌታዬ ፡ ክብርህን ፡ አሳየኝ
ክብርህን ፡ ያዩ ፡ አባቶቼ
ለአንተ ፡ የኖሩትን ፡ ኑሮ ፡ አይቼ
እየዋለ ፡ እያደር ፡ የጠማኝ
ክብርህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የራበኝ
ምን ፡ ዓይነት ፡ እሳት ፡ ነው ፡ ሙሴ ፡ ያየው
ምን ፡ ዓይነት ፡ ብርሃን ፡ ነው ፡ ጳዎሎስ ፡ ያየው
ምንድነው ፡ ጌታዬ ፡ የነካቸው
ለአንተ ፡ እንዲኖሩ ፡ ያረጋቸው
ደስታን ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያሰበው
ሰላምን ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያሰበው
ሊያድነኝ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የመጣው
ሊያድነኝ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የመጣው
ለዚህ ፡ እኮ ፡ነው ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠው
ለዚህ ፡ እኮ ፡ ፡ ነው ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠው
አመልከዋለሁ ፡ ጌታዬን
አመልከዋለሁ ፡ አምላኬን
አመልከዋለሁ ፡ ጌታዬን
አመልከዋለሁ ፡ አምላኬን
ባወራ ፡ ስለእርሱ ፡ ብናገር ፡ ስለእርሱ
ባስብም ፡ ስለእርሱ ፡ ብተርክ ፡ ስለእርሱ
ይሄ ፡ ነው ፡ ሃሳቡ ፡ የእርሱ ፡ የንጉሱ
ባወራ ፡ ስለእርሱ ፡ ብናገር ፡ ስለእርሱ
ባስብም ፡ ስለእርሱ ፡ ብተርክ ፡ ስለእርሱ
ይሄ ፡ ነው ፡ ሃሳቡ ፡ የእርሱ ፡ የንጉሱ
ውበቱን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጥሪዬ
ግርማውን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጥሪዬ
ውበቱን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጥሪዬ
ግርማውን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጥሪዬ
ባወራ ፡ ስለእርሱ ፡ ብናገር ፡ ስለእርሱ
ባስብም ፡ ስለእርሱ ፡ ብተርክ ፡ ስለእርሱ
ይሄ ፡ ነው ፡ ሃሳቡ ፡ የእርሱ ፡ የንጉሱ