amharic gospel mezmur

አዝ፦ ጉድለቴን ፡ ሸፍነህ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ
ያን ፡ ሁሉ ፡ ሸለቆ ፡ አዝለህ ፡ ያሻገርከኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
አባብዬ ፡ ተባረክልኝ (፪x)

ማዳን ፡ በማይችሉት ፡ እኔስ ፡ አልመካም
አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ
አንተ ፡ ነህ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ጌታ
አንተ ፡ ነህ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ጌታ
አንተ ፡ እኮ ፡ ጌታ (፪x) ፤ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ (፪x)

ከንጉሥ ፡ ገበታ ፡ የማይገባኝን (፪x)
ሁሉ ፡ በድካሜ ፡ የተጸየፈኝን (፪x)
ከማዕድን ፡ መሃል ፡ አስቀምጠኸኛል (፪x)
ኦ ፡ ኢየሱሴ ፡ ፍቅርህ ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ አድርጐኛል ፤ ምን ፡ ብል ፡ ያረካኛል

ተባረክልኝ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ተባረክልኝ
ከፍ ፡ በልልኝ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

አዝ፦ ጉድለቴን ፡ ሸፍነህ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ
ያን ፡ ሁሉ ፡ ሸለቆ ፡ አዝለህ ፡ ያሻገርከኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
አባብዬ ፡ ተባረክልኝ (፪x)

ተራራ ፡ ስወጣ ፡ ጉልበት ፡ እየሆንከኝ (፪x)
ስወድቅ ፡ ስነሳ ፡ እየደጋገፍከኝ (፪x)
አቤት ፡ በአንተ ፡ ብርታት ፡ ስንቱን ፡ አልፌያለሁ (፪x)
በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ ፤ ዛሬ ፡ ደርሻለሁ

ተባረክልኝ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ተባረክልኝ
ከፍ ፡ በልልኝ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

ትላንትን ፡ አልፌ ፡ እዚህ ፡ እኮ ፡ መድረሴ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ በራሴ (፪x)
ትላንትን ፡ አልፌ ፡ እዚህ ፡ እኮ ፡ መድረሴ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ በራሴ (፪x)
አይደለም ፡ በራሴ ፡ በራሴ ፡ አይደለም ፡ በራሴ (፪x)

አዝ፦ ጉድለቴን ፡ ሸፍነህ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ
ያን ፡ ሁሉ ፡ ሸለቆ ፡ አዝለህ ፡ ያሻገርከኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
አባብዬ ፡ ተባረክልኝ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue