የገባልኝን ፡ ቃል ፡ እስከሚፈፅመው
እግዚአብሔር ፡ ይተጋል
እኔም ፡ አምነዋለሁ (፬x)
የገባልኝን ፡ ቃል ፡ እስከሚፈፅመው
እግዚአብሔር ፡ ይተጋል
እኔም ፡ አምነዋለሁ (፬x)
ፍፁም ፡ የማይገባ ፡ የማይመስል ፡ ነገር
እንደምን ፡ ይሆናል ፡ የተባለ ፡ ቢሆን
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ በቃሉ ፡ የታመነ
እውን ፡ ያደርገዋል ፡ ተስፋ ፡ ከእርሱ ፡ ካለ
ስለዚህ ፡ አምላኬን ፡ እጠብቃለሁኝ
እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ እኔም ፡ እስካየው (፪x)
ቀናቶች ፡ ቢረዝሙ ፡ ችግሩም ፡ ቢበዛ
እምነቴም ፡ ቢፈተን ፡ ጠላትም ፡ ቢነሳ
ቃል ፡ ተናግሯልና ፡ ይሆናል ፡ አይቀርም
ጌታዬ ፡ ሲከፍተው ፡ ማንም ፡ አይዘጋውም
ስለዚህ ፡ አምላኬን ፡ እጠብቃለሁኝ
እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ እኔም ፡ እስካየው (፪x)
ዓይኖቹ ፡ ያዩኛል ፡ ጆሮውም ፡ ይሰማኛል
የልቤን ፡ ጥያቄ ፡ ጌታዬ ፡ ያውቀዋል
መልስ ፡ እስከሚመጣ ፡ እስከሚጐበኘኝ
አፅንቶ ፡ የሚያቆም ፡ የተስፋ ፡ ቃል ፡ አለኝ
ስለዚህ ፡ አምላኬን ፡ እጠብቃለሁኝ
እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ እኔም ፡ እስካየው (፪x)