Simih Endemifes Zeit new (ሥምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው)

ስምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ
መልካም ፡ መዓዛ ፡ አለው ፡ ውዴ ፡ ሆይ
መልካም ፡ መዓዛ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ ሆይ

ስምህን ፡ ጠርተን ፡ ተፈውሰናል
ካለብን ፡ ደዌ ፡ ነጻ ፡ ወጥተናል
ጅማታችንን ፡ ስምህ ፡ አራሰው
ልባችን፡ ሞልቷል ፡ ሃሌሉያ ፡ ነው
ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ ተመስገንልን
አፍቅረንሃል ፡ ከውስጥ ፡ ከልብ
ጎልማሳነታችንም ፡ ታድሷል
በስምህ ፡ ብርታት ፡ ነጻ ፡ ወጥተናል

አይምሮ ፡ አርሶ ፡ ከልብም ፡ አልፎ
ያለ ፡ ሁኔታ ፡ ተድላን ፡ አልብሶ
የሚጣፍጠው ፡ ሥምህ ፡ ቁልፍ ፡ ነው
ደናግል ፡ ለአንተ ፡ በፍቅር ፡ ናቸው
ሌሊት ፡ በምሽት ፡ ከእንቅልፍ ፡ ተነስተን
ስንበረከክ ፡ አንተን ፡ ፈልገን
ስምህን ፡ ጠርተን ፡ እፎይ ፡ እረካን
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል

ማድጋችንን ፡ ዘይትህ ፡ ሞላው
ያንን ፡ ስምህን ፡ ታምነን ፡ ስንጠራው
ባዶ ፡ ነበር ፡ ማስሮ ፡ ዕቃችን
ግን፡ አሁን ፡ በአንተ ፡ አገኘን
ለጎረቤትም ፡ ተርፏል ፡ ሰላምህ
ከእኛም ፡ አልፎ ፡ ከደናግልህ
። ኦ፡ ምንልህ ፡ የምንሰጥህ
የለንምና ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ስምህ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast
Buy Me a Coffee Button Buy Wongelnet a Coffee

If you appreciate the work we do at Wongelnet and would like to support our ongoing development, research, and the efforts of our support staff, we’d be incredibly grateful if you could buy us a coffee.

Your support not only helps us keep the lights on but also fuels our passion to continue improving the platform and providing you with the best possible service. Every little bit helps us stay focused on delivering the features and updates that matter most to you.


Thank you for being a part of our journey!
You can now buy us a coffee! You can now buy us a coffee

Advertise Here



:: / ::
::
/ ::

Queue