እየዋለ ፡ እያደር (Eyewale Eyader) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

አዝ:- ሁሉን ፡ አድርገህልኛል ፡ የቀረብኝም ፡ የለም
ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም
ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም (፪x)

የሰማይን ፡ ፀጋ ፡ የምድርን ፡ በረከት
በሌላ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ ያገኘሁት
ጽድቅና ፡ ሰላምን ፡ የመንፈስን ፡ ደስታ
አጎናጽፈኅኛል ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ (፪x)

አዝ:- ሁሉን ፡ አድርገህልኛል ፡ የቀረብኝም ፡ የለም
ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም
ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም (፪x)

ምን ፡ ያጠያይቃል ፡ መልካምነትህ
ለኔስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በረከቴ ፡ ነህ
መወደድ ፡ ስይንስህ ፡ ነው ፡ መች ፡ ይበዛብሃል
እንኳን ፡ እኔነቴ ፡ ዘሬ ፡ የገዛልሃል

እየዋለ ፡ እያደር ፡ ታምራትህ ፡ በዛ
የነገስታት ፡ ንጉስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x)

ምን ፡ እንልሃለን ፡ ማዳንህን ፡ እያየን
በምስጋና ፡ በላይ ፡ ምስጋናን ፡ እንሰዋለን
ምን ፡ እንልሃለን ፡ ምሕረትህን ፡ እያየን
በክብርም ፡ በላይ ፡ ክብርን ፡ እንሰጣለን

መልካምን ፡ ማድረግ ፡ ማይታክትህ
አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ ቸርነትህ ፡ አሃሃ
ትላንት ፡ ያረከው ፡ ሳይበቃህ
ዛሬም ፡ ደገምከኝ ፡ አብዝተህ (፪x)

በክብር ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ በክብር ፡ ላይ ፡ አሃ
ቆርጫለሁ ፡ ለመጨመር ፡ ከዚያም ፡ በላይ
አንደበቴን ፡ በምስጋና ፡ እየከፈትኩ ፡ ኦሆ
ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አመጣለሁ

እየዋለ ፡ እያደር ፡ ታምራትህ ፡ በዛ
የነገስታት ፡ ንጉስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x)

ምን ፡ እንልሃለን ፡ ማዳንህን ፡ እያየን
በምስጋና ፡ በላይ ፡ ምስጋናን ፡ እንሰዋለን
ምን ፡ እንልሃለን ፡ ምሕረትህን ፡ እያየን
በክብርም ፡ በላይ ፡ ክብርን ፡ እንሰጣለን

ተራሮችንም ፡ ትክክል ፡ አደረክና ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ
የነሃሱን ፡ ደጆች ፡ ሰባብረህ ፡ እኔን ፡ ለክብር ፡ አበቃህ (፪x)

በክብር ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ በክብር ፡ ላይ ፡ አሃ
ቆርጫለሁ ፡ ለመጨመር ፡ ከዚያም ፡ በላይ
አንደበቴን ፡ በምስጋና ፡ እየከፈትኩ ፡ ኦሆ
ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አመጣለሁ

አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
ንጉሴ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው ፡ አምባዬ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue