አዝ፦ ብዙ (፫x) ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ለአምላኬ ፡ የምሰጠው
ብዙ (፫x) ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ለእርሱ ፡ የምዘምረው (፪x)
ጌታ ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ፡ ነው (፬x)
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
ዙሪያሽ ፡ በሚሆነው ፡ ከቶ ፡ አትታወኪ
የሁሉ ፡ የበላይ ፡ ገዢ ፡ አምላክ ፡ ነውና
በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ ፡ ሰዊለት ፡ ምሥጋና (፪x)
አዝ፦ ብዙ (፫x) ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ለአምላኬ ፡ የምሰጠው
ብዙ (፫x) ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ለእርሱ ፡ የምዘምረው (፪x)
ጌታ ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ፡ ነው (፬x)
በገናም ፡ ይነሳ ፡ እኔም ፡ ማልጄ ፡ እነሳለሁ
ለወደደኝ ፡ ለእርሱ ፡ ቅኔ ፡ እቀኛለሁ
አፌን ፡ በምሥጋና ፡ በቅኔ ፡ ለሞላው
የምለው ፡ የለኝም ፡ ከምሥጋና ፡ ሌላ (፪x)
አዝ፦ ብዙ (፫x) ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ለአምላኬ ፡ የምሰጠው
ብዙ (፫x) ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ለእርሱ ፡ የምዘምረው (፪x)
ጌታ ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ፡ ነው (፬x)
የኢየሱስን ፡ ማዳን ፡ ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ተውቀዋለች
የመስቀሉን ፡ ፍቅር ፡ አይታ ፡ ተማርካለች
ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ወደ ፡ ድንቅ ፡ ብርሃን
አውጥቶኛልና ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)
አዝ፦ ብዙ (፫x) ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ለአምላኬ ፡ የምሰጠው
ብዙ (፫x) ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ለእርሱ ፡ የምዘምረው (፪x)
ጌታ ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ፡ ነው (፬x)
ክብሩ ፡ ሰማያትን ፡ ምድርን ፡ ሁሉ ፡ የሸፈነ
ከአጥናፍ ፡ እስከ ፡ አጥናፍ ፡ ሥሙ ፡ የገነነ
አምላካዊ ፡ ክብሩን ፡ ትቶ ፡ የፈለገኝ
ልሰዋ ፡ ምሥጋና ፡ በዝማሬ ፡ ልቀኝ (፪x)
አዝ፦ ብዙ (፫x) ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ለአምላኬ ፡ የምሰጠው
ብዙ (፫x) ዝማሬ ፡ አለኝ ፡ ለእርሱ ፡ የምዘምረው (፪x)
ጌታ ፡ እርሱ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ፡ ነው (፬x)