Ante Gen Geta Hoy (አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ)

በተዘረጋ ፡ ክንድ ፡ በበረታችም ፡ እጅ
በጌታ ፡ መዳኑን ፡ ከሞት ፡ ከሲዖል ፡ እጅ
እንደምን ፡ ዘንግቶ ፡ ሰው ፡ ያጉረመርማል
ወንድሙን ፡ ለመውገር ፡ እጁን ፡ ይዘረጋል

አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ
ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ
ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ
ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)

ስፍራውን ፡ ለቆ ፡ ሲሄድ ፡ ለመጉደፍ ፡ ሲቸኩል
ትህትናውን ፡ አውልቆ ፡ ለሞት ፡ ሲንቀለቀል
እዪት ፡ ያንን ፡ ዝንጉ ፡ ቃል ፡ ኪዳኑን ፡ ሲያፈርስ
በአመጻው ፡ ብዛት ፡ ፍቅርን ፡ ሲያቀዘቅዝ

አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ
ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ
ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ
ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)

አንተን ፡ እየፈራሁ ፡ ቀኑን ፡ ሁሉ ፡ ልኑር
ትህትናም ፡ አይራቀኝ ፡ አልነፈግህ ፡ ክብር
እጅህ ፡ እንዳይመታኝ ፡ አጉል ፡ ደፋር ፡ ሆኜ
መተረቻ ፡ እንዳልሆን ፡ በሃፍረት ፡ ተከድኜ

አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ
ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ
ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ
ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue