Dagmawi Tilahun--Geta Ale Kegone - Yenen Kifu Lematiwed (የእኔን ፡ ክፉ ፡ ለማትወደው)

ስራመድ ፡ በሞት ፡ ጐዳና
ድካሜን ፡ ከላይ ፡ አየና
ለወጠው ፡ የኔን ፡ ፍፃሜ
ላምልከው ፡ በቀረኝ ፡ ዕድሜ (፪x)

ላምልከው ፡ በቀረኝ ፡ ዕድሜ (፬x)

አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
ዝማሬዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
የእኔን ፡ ክፉ ፡ ለማትወደው (፭x)

ስከተል ፡ የማይጠቅመውን
ሳላውቀው ፡ ክፉና ፡ ደጉን
አንተ ፡ ነህ ፡ የሰበሰብከኝ
ማረፊያ ፡ ጥላ ፡ የሆንከኝ (፭x)

አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
ዝማሬዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
የእኔን ፡ ክፉ ፡ ለማትወደው (፭x)

ሳነባ ፡ ልቤ ፡ ሲከፋ
ስጐተት ፡ በጠላት ፡ ተስፋ
ሰው ፡ አይደል ፡ የደረሰልኝ
እጅህ ፡ ነው ፡ ከሞት ፡ ያስጣለኝ (፭x)

አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
ዝማሬዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው
የእኔን ፡ ክፉ ፡ ለማትወደው (፭x)

ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ ለሥምህ ፡ ልዘምር
ሁልጊዜ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሁልጌዜ ፡ ላምልክህ ፡ ኢየሱሴ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አልኖር ፡ ከአንተ ፡ ርቄ
ወዳጄ ፡ ወዳጄ ፡ ወዳጄ ፡ ላምልክህ ፡ ፈቅጄ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue