Endalkachew Hawaz--Egzabher Tilk New--ስሙን ፡ አከብራለሁ

በሃዘን ፡ ፈንታ ፡ ደስታ
በለቅሶም ፡ ምትክ ፡ ዕልልታ
ሁሉንም ፡ መልካም ፡ አደረገው
ክፉውን ፡ ለበጐ ፡ ቀየረው (፪x)

አዝ፦ ምን ፡ ልበል ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ፡ ለጌታ ፡ ላሰማ (፪x)
በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (፪x)
እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው
እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው

የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፈተው
የነሃሱንም ፡ መዝጊያ ፡ ሰበረው
መወርወሪያዎቹን ፡ ቆራርጦ
አሳለፈኝ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶ

አዝ፦ ምን ፡ ልበል ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ፡ ለጌታ ፡ ላሰማ (፪x)
በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (፪x)
እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው
እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው

በከበረው ፡ ደሙ ፡ ቀድሶ
መንፈሱን ፡ በላዬ ፡ አፍሶ
ሕይወቴን ፡ በፍቅሩ ፡ ቀየረው
ታሪኬን ፡ እንዲህ ፡ አሳመረው (፪x)

አዝ፦ ምን ፡ ልበል ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ፡ ለጌታ ፡ ላሰማ (፪x)
በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ
በምሥጋና ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ
እጅግ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያደረገው ፣ ለእኔ ፡ ያደረገው (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue