Endegziabher Yale manim Yelem (እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም)

(እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም) (፪x)
እያልኩ ፡ አወራለሁ ፡አወራለሁ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ እይቻለሁ) (፪x)

እናቴ ፡ በቅርጫት ፡ ጠቅልላ ፡ ስትጥለኝ
ፈርኦንን ፡ ፈርታ ፡ ባሕር ፡ ላይ ፡ ስትተወኝ
አግዚአብሄር ፡ እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ አሞቀኝ
እንዳልጠፋ ፡ እንዳልሞት ፡ አቅፎ ፡ አተረፈኝ
በድንገት ፡ ሳላውቀው ፡ ፈርኦን ፡ ቤት ፡ ገባሁ
ምንም ፡ ሳይጐልብኝ ፡ በእናቴ ፡ ጡት ፡ አደኩ
እብራይስጥ ፡ እያለሁ ፡ የግብጽ ፡ ይሁን ፡ ተባልኩ
በወግ ፡ በመዓረግ ፡ አደኩኝ ፡ በለጽኩ
ይህንን ፡ ሁሉ ፡ አለፍኩ ፡ ያን ፡ ሁሉ ፡ አዋቂ ፡ ነው
ህዝቡን ፡ አንድመራ ፡ ለካስ ፡ ላላማው ፡ ነው
(በልጅነት ፡ ዘመን ፡ ሲመራኝ ፡(ሲያግዘኝ) እያየሁ
ማንም ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሆንም ፡ እላለሁ) (፪x)

አዝ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ

ግብጻዊውን ፡ ገድዬ ፡ በረሃ ፡ ስገባ
ውኃ ጥም ፡ ሲፈጀኝ ፡ የምበላው ፡ ሳጣ
እንዳልተከበርኩኝ ፡ደግሞ ፡ እረኛ ፡ ስሆን
ኑሮዬን ፡ ጠልቸው ፡ሳማርር ፡ ጌታዬን
ጭራሹን ፡ መጣና ፡ በሽምግልናዬ
እግዚአብሄር ፡ ጠራኝ ፡ እኔ ፡ በቃ ፡ ብየ
ባደኩበት ፡ ኑሮ ፡ ቤቴ ፡ ተመልሼ
ከፈርኦን ፡ ገጠምኩ ፡ በትሬን ፡ በእጄ ፡ ይዤ
ለካስ ፡ ለታሬክ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ያስቀመጠኝ
ከባሕር ፡ አንስቶ ፡ በቤቱ ፡ ሊሾመኝ
(በሽምግልናዬ ፡ ሲመራኝ ፡ሲያግዘኝ) እያየሁ
ማንም ፡እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሆንም ፡ እላለሁ) (፪x)

አዝ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ

ይህን ፡ ሁሉ ፡ አለፍኩ ፡ ያን ፡ ሁሉ ፡ አዋቂ ፡ ነው
ህዝቡን ፡ እንድመራ ፡ ለካስ ፡ ለአላማው ፡ ነው
በልጅነት ፡ ዘመን ፡ ሲመራኝ ፡ እያየሁ
ማንም ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሁንም ፡ እላለሁ
ለካስ ፡ ለታሬክ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ያስቀመጠኝ
ከባሕር ፡ አንስቶ ፡ በቤቱ ፡ ሊሾመኝ
(በሽምግልናዬ ፡ ሲመራኝ ፡ሲያግዘኝ) እያየሁ
ማንም ፡እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይሆንም ፡ እላለሁ) (፪x)

አዝ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue