Yilal Gena (ይላል ፡ ገና)

አምላኬ ፡ እድሌ ፡ ፈንታዬ
ያለመለምከው ፡ ተስፋዬን
መሞት ፡ ሲገባኝ ፡ ኩነኔ
እኔስ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ (፪x)

ገረመኝ ፡ መዳኔ ፡ መዳኔ ፡ ገረመኝ ፡ መዳኔ (፪x)

ውለታ ፡ ያለበት ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል
ፍቅሩን ፡ የቀመሰ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል

ያደረግልኝን ፡ ጌታ ፡ ይሆነልኝን
አስቤው ፡ ያን ፡ ዘመን ፡ በርሱ ፡ ያለፍኩትን

ክበር ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ
ክበር ፡ ልበለው ፡ አከብረዋለሁኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ አነግሰዋለሁኝ

ቅጥቅጥ ፡ ሸንበቆ ፡ አትሰብርም
የወደቀ ፡ አይተህ ፡ አታልፍም
አልቀረሁ ፡ ምስኪን ፡ ተብዬ
ባንተ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ ጌታዬ (፫x)

ቃሉን ፡ ያሰበ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል
ከሞት ፡ ያመለጠ ፡ መች ፡ ውስጡ ፡ ዝም ፡ ይላል
እየደጋገመ ፡ ምሥጋና ፡ ያሰማል

ያደረግልኝን ፡ ጌታ ፡ ይሆነልኝን
አስቤው ፡ ያን ፡ ዘመን ፡ በርሱ ፡ ያለፍኩትን

ክበር ፡ ልበለው ፡ እየደጋገምኩኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ እየደጋተምኩኝ
ክበር ፡ ልበለው ፡ አከብረዋለሁኝ
ንገሥ ፡ ልበለው ፡ አነግሰዋለሁኝ

ቤቴ ፡ በክብሩ ፡ ተሞላና
እኔም ፡ ወግ ፡ አየሁ ፡ እንደገና (፪x)

ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
ሳልሰለች ፡ በደስታ ፡ ልዘምር ፡ ለጌታ

ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ ምነው ፡ በሆንኩለት (፫x)
ሕይወቴ ፡ ያማረው ፡ እርሱን ፡ ያገኘሁ ፡ እለት (፫x)
አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና (፫x)
በቅቶኝ ፡ አልቀመጥ ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና (፫x)

ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና
ይላል ፡ ገና ፡ ውስጤ ፡ ይላል ፡ ገና (፪x)

ይላል ፡ ገና ፡ ምሥጋና
ይላል ፡ ገና ፡ ገናና
ይላል ፡ ገና ፡ አምልኮ
ይላል ፡ ገና ፡ ዝማሬ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue