Zufanih Yezelalem New (ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው)

አመታቶችህ ፡ ከቶ ፡ አያልቁም
የዘመንህ ፡ ቁጥር ፡ አይመረመርም
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ንጉስ ፡ ነህ ፡ ለእኛ

አዝ:- ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው
መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው
አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም
ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x)

ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ መንግስት ፡ የአንተ ፡ ነው
አምላክና ፡ አባት ፡ አዳኝ ፡ የሆንከው
የሲኦልን ፡ ቁልፍ ፡ በእጅህ ፡ ይዘሃል
ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል

አዝ:- ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው
መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው
አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም
ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x)

ከጥንት ፡ ጀምሮ ፡ ምድርን ፡ መሰረትክ
በእጆች ፡ ሥራ ፡ ሰማይን ፡ ሰራህ
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ
ሁሉም ፡ ያልፋሉ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነው

አዝ:-ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው
መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው
አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም
ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x)

ከስሞች ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ስም ፡ ይዘህ
በአባትህ ፡ ቀኝ ፡ በክብር ፡ ያለህ
የሁሉ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ንጉስ
የእኛም ፡ መድሃኒት ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ

አዝ:- ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው
መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው
አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም
ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue