Meserete Kirstos Choir-Hallelujah (ሃሌሉያ)

ገና ፡ ተጓዝ ፡ ነኝ ፡ የሩቅ ፡ አገር ፡ ሰው
በጌታዬ ፡ ቤት ፡ ስደርስ ፡ የማልፈው
በጉን ፡ በግርማ ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ሳየው
በዚያ ፡ እኖራለሁ ፡ ሆኜ ፡ አዲስ ፡ ሰው
እስከዚያች ፡ ቀን ፡ ግን ፡ በጣም ፡ እተጋለሁ
መከራም ፡ ቢኖር ፡ በሥሙ ፡ አልፋለሁ

አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ሃሌሉያ ፡ ሁሉን ፡ ችለሃል
ሃሌሉያ ፡ ዮርዳኖስንም
ሃሌሉያ ፡ ክንድህ ፡ ከፈለው
ማዕበሉን ፡ ደግሞ ፡ ቃልህ ፡ አዘዘው

ብደክም ፡ ብዝል ፡ ብወድቅ ፡ ብነሳ
ስማቅቅ ፡ ብኖር ፡ ከእርሱ ፡ አልለይም
የአሁን ፡ ክሳቴ ፡ ጉስቁልናዬ
ሁሉም ፡ አይኖርም ፡ ሳገኝ ፡ ጌታዬን
አንድ ፡ ቀን ፡ ከጽዮን ፡ ድምጹን ፡ ስሰማ
እበረታለሁ ፡ ሁሉም ፡ ያልፍና

አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ሃሌሉያ ፡ ሁሉን ፡ ችለሃል
ሃሌሉያ ፡ ዮርዳኖስንም
ሃሌሉያ ፡ ክንድህ ፡ ከፈለው
ማዕበሉን ፡ ደግሞ ፡ ቃልህ ፡ አዘዘው

ትላንት ፡ ተዋግቶ ፡ ነፍሴን ፡ ካዳናት
ዛሬ ፡ የሚታክት ፡ አምላክ ፡ መች ፡ አላት
አይለወጥም ፡ ዛሬም ፡ ኃያል ፡ ነው
በእውነት ፡ አምላኬ ፡ የድል ፡ ጌታ ፡ ነው
ስለዚህ ፡ ጠላት ፡ ተስፋህ ፡ ይደምሰስ
ነው ፡ መሠረቴ ፡ አለት ፡ የማይፈርስ

አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ሃሌሉያ ፡ ሁሉን ፡ ችለሃል
ሃሌሉያ ፡ ዮርዳኖስንም
ሃሌሉያ ፡ ክንድህ ፡ ከፈለው
ማዕበሉን ፡ ደግሞ ፡ ቃልህ ፡ አዘዘው (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue