Maranatha Gieta (ማራናታ ፡ ጌታ)

አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x)

አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x)

በቀስተ ፡ ዳመና ፡ ከሰማይ ፡ ይመጣል
ተሞሽረሽ ፡ ቆይው ፡ አክብሮ ፡ ይወስድሻል
የሰርጉ ፡ ቀን ፡ ቀርቧል ፡ ልብስሽን ፡ እጠቢ
እንዳለሽ: ሁኚለት: ተይ: ገሸሽ: አትበይ
ውዴ ፡ ውዴ ፡ እያለ ፡ በናፍቆት ፡ እየጠራ
ወደ ፡ አንች ፡ ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ በዳመና (፪x)

አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x)

የሰርግሽን ፡ ዕለት ፡ ዘንግተሽ ፡ ከሆነ
ዛሬ ፡ ተዘጋጂ ፡ ዘመኑ ፡ ቀረበ
ምልክቶች ፡ ሞልተው ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠበቃል
አይዘገይም ፡ ደግሞ ፡ በፍጥነት ፡ ይመጣል
ማራናታ ፡ እያልሽ ፡ ያለቀሽው ፡ እንባ
ይታበሳል ፡ ፈጥኖ ፡ ልብሽ ፡ ብቻ ፡ ይጥና (፪x)

አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x)

አንቺን ፡ ፈልገውሽ ፡ በዙሪያሽ ፡ ሚያደቡ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ፡ ለመዋጥ ፡ የጓጉ
ድንግልናሽን ፡ ግን ፡ አጥብቀሽ ፡ ጠብቂ
ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ ቁሚ ፡ ተጠንቀቂ
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ እውነተኛው፡ መሲህ
ሊመጣ ፡ ነውና ፡ ልብስሽን ፡ እጠቢ (፪x)

አዝ፦ ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ማራናታ
ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ማራናታ
ናፍቆቴ ፡ ናና ፡ ናፍቆቴ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue