Meserete Kirstos Choir--Endet Dink Amlak New--Endet Dink Amlak Neh (እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው)

የደን ፡ ልማቱ ፡ የገደል ፡ ስርገቱ
የወንዝ ፡ እርዝመቱ ፡ የቀላይ ፡ ውበቱ
የቆንጆ ፡ ገጽታው ፡ የቦታው ፡ ከፍታው
የባሕር ፡ ጥልቀቱ ፡ የሜዳ ፡ ስፋቱ
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)

የሽቶ ፡ መዓዛው ፡ የሙዚቃ ፡ ቃናው
የለምለም ፡ እርካታው ፡ የመዝናኛ ፡ ቦታው
የመፋቅር ፡ ወዙ ፡ የትዳር ፡ ማገዙ
የፍጥረት ፡ ድምቀቱ ፡ የሰማይ ፡ ርቀቱ
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)

የአበቦች ፡ ፍካታ ፡ የወፎች ፡ ጫጫታ
የቀለም ፡ መዋሃድ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ መዋደድ
የእምነት ፡ እርካታ ፡ ሰላምና ፡ ደስታ
የፅዮን ፡ ውበቱ ፡ የእውነት ፡ ጥራቱ
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)

ጐህ ፡ ሲቀድ ፡ ማለዳ ፡ ጨለማ ፡ ሲከዳ
የፀሐዩ ፡ ሙቀት ፡ የከዋክብት ፡ ብዛት
የደመናት ፡ ክምር ፡ ንጹህ ፡ ተስማሚ ፡ አየር
ሁሉን ፡ በስርዓት ፡ መሪ ፡ ለፍጥረቱ
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው
እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት
የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue