ባለፀጋ

አዝ፦ በምሕረቱ ፡ ባለፀጋ ፡ ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኝ
እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ አፀደቀኝ (፪x)

ምንድነው ፡ ያቆመኝ ፡ ከፃድቃኖች ፡ ስፍራ
ስለ ፡ ምህረትህ ፡ ልናገር ፡ ላወራ
ለካስ ፡ ከማህፀን ፡ ጌታዬ ፡ አስቦኛል
ያን ፡ ሁሉ ፡ ኀጢአቴን ፡ በደሙ ፡ አጥቦልኛል

አዝ፦ በምሕረቱ ፡ ባለፀጋ ፡ ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኝ
እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ አፀደቀኝ (፪x)

እንዴት ፡ አደረገኝ ፡ እኔን ፡ አዲስ ፡ ፍጥረት
በመንፈሱ ፡ ገዛኝ ፡ ጌታዬ ፡ በእርሱ ፡ እምነት
ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ፍቅሩ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል
አዲስ ፡ ሰው ፡ መሆኔ ፡ ሁሌም ፡ ይደንቀኛል

አዝ፦ በምሕረቱ ፡ ባለፀጋ ፡ ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኝ
እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ አፀደቀኝ (፪x)

ፀጋው ፡ በእምነት ፡ እኔን ፡ አድኖኛል
የእግዚአብሔር ፡ ስጦታ ፡ በእርግጥ ፡ በዝቶልኛል
ታዲያ ፡ ምን ፡ አለና ፡ ከእኔ ፡ የምለው ፡ ሥራ
ታላቅነትህን ፡ ደፍሬ ፡ ላወራ

አዝ፦ በምሕረቱ ፡ ባለፀጋ ፡ ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኝ
እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ አፀደቀኝ (፪x)

እንደ ፡ ኀጢአቴ ፡ ብዛት ፡ ጌታዬ ፡ አላረገብኝ
እንደ ፡ በደሌም ፡ ከቶ ፡ አልከፈለኝ
ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ እግዚአብሔር ፡ ወዶኛል
ምሕረት ፡ ቸርነቱ ፡ ፀጋው ፡ በዝቶልኛል

አዝ፦ በምሕረቱ ፡ ባለፀጋ ፡ ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከወደደኝ ፡ ፍቅሩ ፡ የተነሳ
ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኝ
እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ አፀደቀኝ (፪x)

ፍቅሩ ፡ በዝቶልኛል
ምህረት በዝቶልኛል
ፀጋው ፡ በዝቶልኛል
ሰላም ፡ በዝቶልኛል (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue