በአዲስ ፡ ሕይወት ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
በሰላም ፡ በደስታ ፡ በፍቅር
ኑሮ ፡ ናፍቄያለሁ ፡ ጌታዬ
ቶሎ ፡ ና ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ተስፋዬ
ኦሆሆሆሆሆሆሆ

አዝ፦ ማራናታ ፡ ማራናታ
አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

ባልተሰማ ፡ ቋንቋ ፡ ልናገር
ከቅዱሳኖች ፡ ጋራ ፡ ልዘምር
ይሄ ፡ ነው ፡ ናፍቆቴ ፡ ቶሎ ፡ ና
ውዴ ፡ ሆይ ፡ ኩራቴ ፡ አንተ ፡ ነህና
ኦሆሆሆሆሆሆሆ

አዝ፦ ማራናታ ፡ ማራናታ
አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

አዲሱን ፡ ነኝ ፡ ለብሼ
የታረድከውን ፡ በግ ፡ ዳስሼ
ይህን ፡ ለማየት ፡ ነው ፡ ናፍቆቴ
እባክህ ፡ ቶሎ ፡ ና ፡ አባቴ
ኦሆሆሆሆሆሆሆ

አዝ፦ ማራናታ ፡ ማራናታ
አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

የምድሩ ፡ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ጠቅሞኛል ፡ ጌታዬ ፡ ይኸው ፡ ልናገር
ግን ፡ አሁን ፡ ናፍቆቴ ፡ ይሄ ፡ ነው
ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምለው
ኦሆሆሆሆሆሆሆ

አዝ፦ ማራናታ ፡ ማራናታ
አሜን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue