Addis Zimare Enzemir (አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ እንዘምር)

አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር
ለመድኃኒታችን ፡ ክብር
የምሥጋናችንን ፡ ሽታ
እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x)

በእረኛቸው ፡ የታመኑ ፣ በመስኩ ፡ የተሰማሩ
ዱካውን ፡ እየተከተሉ ፣ ለደህንነት ፡ የተጠሩ
ከጨካኝ ፡ አውሬ ፡ የዳኑ ፣ ከመታረድ ፡ የተረፉ
ሃሴትን ፡ እንደሚያደርጉ ፡ በአጥፊው ፡ ጥፋት ፡ ስላልጠፉ

አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር
ለመድኃኒታችን ፡ ክብር
የምሥጋናችንን ፡ ሽታ
እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x)

ማቃችንን ፡ ቀዷልና ፡ ፀጋውን ፡ አልብሶናልና
ክብራችን ፡ ትዘምርለት ፡ ፍቅሩ ፡ አጽናንቶናልና
ጉዳታችንን ፡ የሚሹ ፡ ጉድጓድ ፡ ምሰው ፡ የጠበቁን
አጋንንት ፡ አፍረዋልና ፡ ያደፈጡት ፡ ሊያጠቁን

አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር
ለመድኃኒታችን ፡ ክብር
የምሥጋናችንን ፡ ሽታ
እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x)

በፍፁም ፡ ልብ ፡ እንዘምር ፣ በአምላካችን ፡ ደስ ፡ ይበለን
እናጨብጭብ ፡ ዕልል ፡ እንበል ፣ ለምንስ ፡ እንቆጥባለን
በምሥጋናችን ፡ ዝማሬ ፡ ምሽጉን ፡ እናፈርሳለን
በመንፈሳዊው ፡ ጦር ፡ ዕቃ ፡ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን

አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር
ለመድኃኒታችን ፡ ክብር
የምሥጋናችንን ፡ ሽታ
እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue