ዘላለም ፡ ድንቅ ፡ ነህ
ዘላለም ፡ ዕጹብ ፡ ነህ
አመልክሃለሁ ፡ ልዩ ፡ ነህ
አመልክሃለሁ ፡ ግሩም ፡ ነህ (፪x)
አቤት ፡ ውበትህ
ግርማ ፡ ሞገስህ (፪x)
ነበልባል ፡ ዓይንህ
አቤት ፡ ማርኮኛል ፡ አስደንቆኛል (፪x)
ውበትህ ፡ ማርኮኛል ፡ አስደንቆኛል (፪x)
አምላክነትህ ፡ ማርኮኝ ፡ እኔን ፡ አመልክሃለሁ
ጌትነትህም ፡ ወርሶት ፡ ልቤን ፡ እገዛልሃለሁ (፪x)
ግርማ ፡ ሞገስህ ፡ ዓይኔን ፡ አልፎ ፡ ልቤን ፡ ነካው
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ለካ (፪x)
አምላክነትህ ፡ ማርኮኝ ፡ እኔን ፡ አመልክሃለሁ
ጌትነትህም ፡ ወርሶት ፡ ልቤን ፡ እገዛልሃለሁ (፪x)
ግርማ ፡ ሞገስህ ፡ ዓይኔን ፡ አልፎ ፡ ልቤን ፡ ነካው
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ለካ (፪x)