እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም (Endante Yale Yelem)

እግዚአብሔርን ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ
ቸርነቱን ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ
ፍቅሩንም ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ
ደግነቱን ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ

አቤቱ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)
አምላኬ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም
ጌታዬ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም

አጥንቶቼ ፡ ሁሉ ፡ እንደዚህ ፡ ይሉሃል
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው ፡ ኦሆሆ
ብለው ፡ ያመልኩሃል (፪x)

ኧረ ፡ እንደው ፡ ምናለ ፡ ቃላት ፡ ባገኘሁኝ ፡ አሃሃ
የልቤን ፡ የውስጤን ፡ ዘርዝሬ ፡ መናገር ፡ በቻልኩኝ (፪x)

እግዚአብሔርን ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ
ቸርነቱን ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ
ፍቅሩንም ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ
ደግነቱን ፡ አሰብኩት ፡ ደስም ፡ አለኝ

አቤቱ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)
አምላኬ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም
ጌታዬ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም

ብዙዎች ፡ ኃይል ፡ አግኝተው ፡ ኦሆሆ
ብዙ ፡ ነገር ፡ አሉህ ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ግን ፡ ትበልጣለህ ፡ አሃሃ
እስከዛሬ ፡ ካሉህ ፡ ኦሆሆ (፪x)

አቤቱ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)
አምላኬ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም
ጌታዬ ፡ አንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም

ኧረ ፡ እንደው ፡ ምናለ ፡ ቃላት ፡ ባገኘሁኝ
የልቤን ፡ የውስጤን ፡ ዘርዝሬ ፡ መናገር ፡ በቻልኩኝ

አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው (፬x)

ድንቅ ፡ ነው ፡ ግርማው ፡ ውበቱ
እግዚአብሔር/አምላኬ ፡ አቤቱ ፡ አቤቱ (፪x)

አጥንቶቼ ፡ ሁሉ ፡ እንደዚህ ፡ ይሉሃል
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው ፡ ብለው ፡ ያመልኩሃል (፪x)

ነፍስም ፡ አልቀረልኝ ፡ አንተን ፡ አይቼ
በፊትህ ፡ ወደኩኝ ፡ ድምጽህን ፡ ሰምቼ
ውበትህ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ያምራል
ሞገስ ፡ በከንፈርህ ፡ ጌታ ፡ ይፈሳል

ድንቅ ፡ ነው ፡ ግርማው ፡ ውበቱ
እግዚአብሔር/አምላኬ ፡ አቤቱ ፡ አቤቱ (፪x)

ከፀሐይ ፡ ሰባት ፡ እጅ ፡ ያበራል ፡ ፊቱ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ማየቱ
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ያለው
ባህሪው ፡ ውበቱ ፡ አስደናቂ ፡ ነው

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue