አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ
በቀጥርም ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ
ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ
አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ
አፌን ፡ በምሥጋና ፡ ሞልተኸዋልና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
እናገር ፡ የምችለውን ፡ ይህን ፡ ነውና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
ያዘነ ፡ በፊትህ ፡ አይገኝምና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
በፊትህ ፡ ቃል ፡ ደስታ ፡ ይጠግባልና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ
በቀጥርም ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ
ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ
አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ
የጐበጠው ፡ ሁሉ ፡ ቀና ፡ ይላልና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ይቻልሃልና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
ለቃልህ ፡ የማይታዘዝ ፡ አንድም ፡ የለምና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
ብቻህን ፡ ተዓምራት ፡ ታደርጋለህና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ
በቀጥርም ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ
ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ
አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ
ሕዝብህ ፡ ወደ ፡ እረፍት ፡ ይገባልና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
እርዳታህም ፡ ከላይ ፡ ይመጣልና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
በሰንበትም ፡ ችግር ፡ አይገኝምና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
ሁሉ ፡ በሚያርፍበት ፡ ትሰራለህና
እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x)
አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ
በቀጥርም ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ
ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ
አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ
ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ
ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ