Geta becha Tamagne new (ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው)

በዓለም ፡ ላይ ፡ ቢዞር ፡ ቢዞር
አይገኝም ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር
መደነቅ ፡ መገርም ፡ ሞላብኝ
አምላኬን ፡ ሳስበው ፡ ደስ ፡ አለኝ (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ብቻ (፬x)
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፫x)

ትናንትና ፡ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም
በጥላ ፡ መዘዋወር ፡ አያውቅም
ታማኝ ፡ እንደሆነ ፡ ይኖራል
የሚታመኑትን ፡ ያኮራል (፪x)

አዝ፦ እርሱ ፡ ብቻ (፬x)
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፫x)

የሚከፍት ፡ ሚዘጋ ፡ የሌለው
ሚዘጋም ፡ የሚከፍትም ፡ የሌለው
ሁሉን ፡ ማድረግ ፡ ፍጹም ፡ የቻለ
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ብቻ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ነው (፫x)
እርሱ ፡ ብቻ ፡ አዳኝ ፡ ነው (፫x)
ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፫x)

حال ہی میں سنا

0 تبصرے
    کوئی تبصرہ نہیں ملا

:: / ::
::
/ ::

قطار