አዝማች
(የምስራች ፡ የምስራች ፡ ይኸው
የምስራቹ ፡ ጽዮን ፡ ደርሰናል ፡ እና ፡ አትሰልቹ
ያቻት ፡ ባሻገር ፡ የጽድቃችን ፡ አገር) (፪x)
ዘመናትን ፡ ቆጥረን ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል
እንሂድላት ፡ ስዓቱ ፡ ደርሷል
ከተራራው ፡ ጐን ፡ የምትታየው
ጽዮን ፡ ያች ፡ ናት ፡ ድንቋ ፡ ቤታችን
አዝ
የምስራች
ቅጥሯን ፡ ልንረግጥ ፡ ምንም ፡ አልቀረን
እፎይ ፡ ለማለት ፡ ጽዮን ፡ ቤታችን
ከማዶ ፡ ያለው ፡ የአትክልት ፡ ቦታ
የጽዮን ፡ ቤት ፡ ነው፡ የሰጠን ፡ ጌታ
አዝ
የምስራች
ተራራ ፡ ጋርዶን ፡ ሳናያት ፡ ጀንበር
አሁን ፡ ምን ፡ ቀረን ፡ ከጽዮን ፡ ቤት
አቤት ፡ ማማሩ ፡ አበባው ፡ መስኩ
ግምቴ ፡ ይሄ ፡ ነው፡ የውበት ፡ ልኩ
አዝ
የምስራች